Statement of Values & Code of Ethics

አይኤኤፍ እሴቶቹን እና የስነምግባር መርሆዎቹን በሰኔ ወር 2004 እ አ አ በአለም ዙሪያ ከሚገኙ አባላቶቹ ጋር በመመካከር እና መወያየት አዘጋጅቷል

ግቢ

መቻቾች ወገንተኛ ያልሆነ ሚና በመጫወት ቡድኖች የተሻለ ሚና እንዲጫወቱ የሚጋበዙ ናቸው ሂደቱን በመምራት በተሳታፊነት እና ውጤት መካከል ሚዛናዊነት እንዲፈጠር እንሰራለን።

እኛ የአለም አቀፍ አመቻቾች ማህበር (አይኤኤፍ) አባላት ሙያችን በግለሰቦች ህይውት፣በድርጅቶች እና ማህበረሰብ ውስጥ አዎንታዊ አስተዋጽዖ እንድናበረክት ልዩ እድል እንደሚሰጠን እናምናለን ውጤታማነታችን የሚመሰረተው ባለን ሃቀኝነት እና በእኛና ኧብረናቸው የምንሰራቸው መካከል ባለው አመኔታ ነው። በመሆኑም ተግባራችንን የሚመራባቸውን እሴቶቻችንን እና የስነምግባር መርሆዎቻችንን መቅረጽ እና ግልጽ ማድረግ አስፈላጊነት እንረዳለን።

ይህ የእሴቶች እና የስነምግባር መርሆዎች መግለጫ የአይኤኤፍ አባላትን የግል፣ የሙያ እና የባህል ብዝሃነት ጨምሮ  የስራችንን እና የማመቻቸት መስክ ውስብስብ ባህርያትን እንረዳለን የአለም አቀፍ አመቻቾች ማህበር (አይኤኤፍ) አባላት እነዚህን የእሴቶች እና የስነምግባር መርሆዎች ለሙያ ምግባራቸው መመሪያነት ለመጠቀም ቁርጠኛ ናቸው እነዚህ ምርሆዎች የተገለጹት ስነምግባራዊ ልምምድን ለመምራት ሰፋ ባለ መግለጫ ሲሆን ዓላማውም ሰፊ ማዕቀፍ ለመፍጠር እንጂ ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ መመሪያ ለመስጠት አይደለም። እነዚህን እሴቶች እና የስነምግባር መርሆዎች ትግበራ በተመለከተ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቢኖሩ ለአለም አቀፍ አመቻቾች ማህበር (አይኤኤፍ) ሊቀርቡ ይችላሉ

ሴቶች መግለጫ

እን አመቻቾች ስብስብ በግለሰብ የግል ችሎታ እና የቡድን የጋራ ጥበብ ቡድኑ ከእያንዳንዱ አባል ግለሰቦች አስተዋጽኦ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት እናደርጋለን። የራሳችንን የግል አመለካከት ወደ ጎን አድርገን ቡድኑ የራሱን ምርጫዎች/ውሳኔዎች እንዲያደርግ እናበረታታለን። የትብብር እና የመደጋገፍ ግንኙነት የጋራ መግባባትን እንደሚፈጥር እና ትርጉም ያለው ውጤት እንደሚያመጣ እናምናለን።   ሙያዊ ትብብር ለመስኩ መሻሻል ያለውን ጠቀሜታ እናከብራለን።


Download the Statement of Values and Code of Ethics in:  

English          Portugese          Amharic


Code of Ethics

1. ምግር መመሪያ

እኛ ያለነው የማመቻቸት ብቃቶቻችንን ተጠቅመን ለደንበኞቻችን እሴት በመጨመር አገልግሎት ለመስጠት ነው

ደንበኞቻችን የማመቻቸት አገልግሎት የምናበረክትላቸው ቡድኖች እና እነርሱን በመወከል ከእኛ ጋር ውል የሚገቡ ናቸው የደንበኞቻችንን ፍላጎት በመረዳት የሚመጥናቸውን አገልግሎት ለመስጠት እና ቡድኑ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስመዘግብ ከደንበኞቻችን ጋር በቅርበት እንሰራለን ሂደቱን በብቃት መምራት የእኛ ሃላፊነት ነው። ቡድኑ ቅድሚያ በቡድኑ ወይም ተወካዮቹ ከታሰበው አቅጣጫ ሌላ ይዞ ለመሄድ ከፈለገ የኛ ድርሻ የበፊቱን እና አዲሱን አቅጣጫ በማስታረቅ ቡድኑ ወደፊት መቀጠልእንዲችል መርዳት ነው።

 

2. ጥቅም ግጭት

ጥቅም ግጭት ምክንያት የሚሆን ነገር ካለ በግልጽነት እናሳውቃለን

ከደበኞቻችን ጋር ውል ከማድርጋችን በፊት ጥቅም ግጭት፣ የግል አመለካከት ወይም አቋም፣ ከዚህ ቀደም ስለድርጅቱ የምናውቀውና የሁሉንም የቡድን አባላት ጥቅም ባከበረ መለኩ አገልግሎት እንዳንሰጥ የሚያደርግ ምክንያት ካለ በግልጽነት እና በታማኝነት እንወያያለን። ይህን የምናደርገውም በጋራ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመውሰድ እና የደንበኛውንም ሆነ የራሳችንን ተዓማኒነት እና ውጤታማነት ሊጎዳ የሚችል እድል ለመቀነስ ነው። ስልጣናችንን/ሃላፊነታችንን በመጠቀም አግባብ ያልሆነ  እድል፣ ትርፍ ወይም ጥቅም ከማግኘት እንቆጠባለን።

 

3. ቡድን ሉዓላዊንት/ነጻነት

ቡድኑን ባህል፣ መብቶች፣ እና ሉዓላዊነት እናከብራለን

ቱም ላይ ይሁን ለተሳትፎ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ቡድኑን የታሰበበት ስምምነት እንሻለን የታሳታፊዎቹን ደህንነትም ይሁን ክብር አደጋ ላይ የሚጥል፣ የመምረጥ መብታቸውን ወይም የቡድኑን ስራ ተዓማኒነት አደጋ ላይ የሚጥል ማናቸውንም ነገር የግድ አንልም።

 

4. ሂደቶች፣ ዘዴዎች፣ እና መርጃዎች

ሂደቶችን፣ ዘዴዎችን፣ እና መሳሪያዎች በሃላፊነት እንጠቀማለን

ቡድኑ ወይም ተወካዮቹ ጋር በመወያየት ቡድኑ ግቦቹን እንዲመታ የሚያስችሉት ሂደቶችን እንቀርጻለን፥ ብሎም በጣም አግባብነት ያላቸው ዘዴዎችን እና መርጃውችን እናመቻቻለን

 

5. አክብት፣ ደህንነት፣ ፍትሃዊነት፣ እና ታማኝነት

አክብት፣ ደህንነት፣ ፍትሃዊነት፣ እና ታማኝነት

ሁሉም ተሳታፊዎች በነጻነት ሊናገሩበት እና የግለሰቦች ድንበር የሚከበርበት አክብሮት እና ደህንነት የሰፈነበት ከባቢ ለመፍጠር እንጥራለንክህሎቶቻችንን፣ እውቀታችንን፣ መርጃዎቻችንን እና ጥበባችንን የሁሉንም ሰው አስተያየት እድል እንዲያግኝ እና እንዲከበር ለማድረግ እንጠቀምበታለን።

ሁሉም ባለድርሻዎች የመወከል እና መሳተፍ እድል እንዲያገኙ እንጥራለን። በተሳታፊዎች መካከል በሚኖረው ግንኙነት እንዲሁም በተሳታፊዎችና በአመቻቹ መካከል በሚኖሩ ግንኙነቶች ፍትሃዊነትን እናበረታታለን፥ ሁሉም ተሳታፊዎች ሃሳባቸውንና ስሜቶቻቸውንና እንዲመዝኑ ብሎም እንዲያካፍሉ እድል እንዲያገኙ እናደርጋለን። ቡድኑ ከእያንዳንዱ አባል የተፈጥሮ ስጦታዎች፣ መክሊቶች እና የህይወት ልምዶች ተካፋይ እንዲሆን ልዩ ልዩ መንገዶችን በመጠቀም እንሰራለን። የልዩ ልዩ መስተጋብር ዘይቤዎችን ከግንዛቤ ያስገባ ክፍለጊዜዎችን በመቅረጽ ለምሉዕነት እና ራስን መግለጽ አክብሮት ባለው መልኩ እንሰራለን። የምንውስደው የትኛውም እርምጃ በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ እንዳለው እንረዳለን።

 

6. ሂደቱ ባላደራነት

የሂደቱን ባላደራነት እና ይዘት ላይ ወገንተኛ ያለመሆንን እንለማመዳለን/እንተገብራለን።

ተሳታፊዎች የእነርሱን አውድ እውቀት እና ልምድ የሚያመጡ ሲሆን፥ እኛ ደግሞ የቡድን መስተጋብር ሂደትን በተመለከተ እውቀትና ልምድ እናመጣለን። የቡድን ውጤት ላይ ተጽዕኖአችንን ለመቀነስ በንቃት እንጠነቀቃለን። ቡድኑ የሌለው የይዘት እውቀት በሚኖረን ጊዜ እና ቡድኑ ውጤታማ መሆን ሲኖርበት፣ የሚና ለውጥ ልናደርግ እንደሆነ ገልጸን እውቀታችንን ልናካፍል እንችላለን።

 

7. ሚስጢራዊነት

የመረጃ ሚስጢራዊነትን እንጠብቃለን።

የደበኛውን መረጃ በተመለከተ ሚስጢራዊነትን እንጠብቃለን። በመሆኑም የደንበኛውን መረጃ ከድርጅቱ ውስጥም ይሁን ውጪ ለማንም አናካፍልም፤ የቡድንን ይዘት ወይም የግለሰብን አስተያየትም ሆነ ባህርይ የሚመለከተውን ፈቃድ ሳናገኝ ለሌላ አናካፍልም።

 

8. የሙያ እድግት/ልማት

የማመቻቸት ክህሎቶቻችንን እና እውቀታችንን ያለማቋረጥ ማሻሻል የራሳችን ሃላፊነት ነው።

ያለማቋረጥ እንማራለን፤ እናድጋለን። እውቀታችንን እና የማመቻቸት ክህሎታችንን ያለማቋረጥ በማሻሻል እድሎችን በመፍጠር ቡድኖችን በስራቸው በተሻለ እንድናግዛቸው እንጥራለን።

 

 

 

SHARE